ከቡና ወጪ ምርት 2 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል

ከቡና ወጪ ምርት 2 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል

በተያዘው በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ምርት 2 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት    መታቀዱን የኢትጵዮያ ቡናና ሻይ ባለስጣን አስታወቀ፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ÷በተያዘው በጀት ዓመት ከ400 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 2 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መታቀዱን ጠቅሰው ባለፉት ሦስት ወራት 115 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በመላክ 520 ሚሊየን ዶላር ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።

በሦስት ወራቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በበጀት ዓመቱ ለማግኘት የታቀደውን የ2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል አመላካች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ  የተያዘውን  ዕቅድ  ለማሳካት  የቡና ምርትና ምርታማነት መጨመር እንዲሁም ጥራት ያለው ቡና ወደ ገበያ ለማቅረብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጎን ለጎንም የቡና ግብይቱን የሚያሳልጡ አሰራሮችን የመዘርጋትና የገበያ አማራጮችን የማስፋት ሥራዎች በሥፋት እየተከናወኑ  መሆናቸውን ገልፀው በቡና ምርት እሴት የመጨመርና የግብይት ሰንሰለቱን የማሳጠር ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

ጀርመን፣  ጃፓን፣  ሳዑዲ አረቢያ፣ ቤልጂየምና አሜሪካ የኢትዮጵያ የውጭ የቡና ገበያ መዳረሻ ሀገራት ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ቻይና፣ ደቡብ  ኮሪያና ጆርዳን የኢትዮጵያን ቡና በስፋት የሚገዙ ሀገራት እየሆኑ መምጣታቸው ተመላክቷል፡፡

ምንጭ፡-  (ኤፍ ቢ ሲ)

It is planned to earn 2 billion dollars from the production of coffee

The Ethiopian Coffee and Tea Company has announced that it plans to earn $2 billion from coffee production in the current fiscal year.

The director general of the authority, Adugna Debala (Dr.), mentioned that it is planned to earn 2 billion dollars in foreign exchange by supplying more than 400 thousand tons of coffee to the foreign market in the current fiscal year.

He also pointed out that the foreign currency obtained in the three months is an indication that it is possible to achieve the 2 billion dollar income plan planned for the fiscal year.

ESA reported that in order to achieve the plan set for the fiscal year, increasing coffee production and productivity as well as providing quality coffee to the market is being done.

On the other hand, he stated that the activities of developing the procedures to facilitate the coffee trade and expanding the market options are being carried out on a large scale and mentioned that the activities of increasing the value of the coffee product and shortening the marketing chain have been carried out.

Germany, Japan, Saudi Arabia, Belgium, and the United States are the destination countries for Ethiopia’s foreign coffee market, and recently, China, South Korea, and Jordan have become major buyers of Ethiopian coffee.

Translation:- Apex Consult

Translate »
Scroll to Top